- የመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ
ገንዘብ ሳይከፍሉ ለሰዎች ሊያበረክቱ የሚችሉዋቸው ስጦታዎች

‹‹ትልቅ ነገር ማድረግ ቢያቅተን ከፍቅር ጋር ትንሽ ነገር ማድረግ አያቅተንም›› ይላሉ ማዘር ተሬዛ:: በዕለት ተዕለት ውሎአችን ዋጋ (ገንዘብ)የማያስከፍሉ፤ ነገር ግን ለሰዎች እጅግ ዋጋ ያላቸውን ነገሮችን አንድ ያልታወቁ ጸሐፊ እንዲህአስቀምጠዋቸዋል::
የመስማት ስጦታ
ሰዎች ስለጉዳያቸው ወይም ስለችግራቸው ሲያወጉ ከልብ መስማትን የመሰለ ስጦታ የለም:: ታዲያሳናቋርጣቸው፤ በሃሳብ ሌላ ቦታ ሳንሔድ ወይም ስለምንመልስላቸው መልስ ሳናሰላሰል መሆን አለበት:: ዝምብሎ ከልብ ማዳመጥ ብቻ!
ፍቅር የማሳየት ስጦታ
ፍጹም ሳይሰስቱ ከልብ ሰዎችን በመጨበጥና በማቀፍ ለእነርሱ ያለዎትን ፍቅር፤ ትኩረትና አድናቆትይግለጹላቸው::
የሳቅ ስጦታ
በየዕለቱ የሚገጥምዎትን አስደሳች ሁኔታዎች (ጽሑፎች፤ ፎቶዎች፤ ካርቱኖች) በመላክ ደስታዎን (ሳቅዎን) ለሰዎች ያካፍሉ፤ የሌሎችንም ደስታ ወይም ሳቅ እንዲሁ ይካፈሉ::
የጽሑፍ ስጦታ
ሰዎች ስላደረጉልዎ መልካም ነገር ምስጋናዎን በራስዎ የእጅ ጽሑፍ በመጻፍ ይስጧቸው፤ የዚህ ዓይነትጽሑፎች ዘመን ከመሻገራቸውም በላይ ሕይወት ይቀይራሉ::
የምስጋና ስጦታ
ሰዎች ለሠሩት ሥራ ወይም ላደረጉት ለውጥ ‹‹ትልቅ ሥራ ሠርተሻል››፤ ‹‹ዛሬ በጣም አምሮብሃል››፤‹‹በጣም ቆንጆ ምግብ ሠርተሻል››ወዘተ.. በማለት አድናቆትዎን ይግለጹ ይህን ዓይነት እውነተኛ አድናቆት የሰዎችን ቀን ብሩህ ያደርጋል:: መልካም ውለታ የማድረግ ስጦታ ከዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎ ወጣ ይበሉና ለሚወዱዋቸው ሰዎች ያልተጠበቀ ድርጊት በመፈጸም ያስደንቋቸው:: አረጋውያንን መጠየቅ፤ ሕፃናትን ማጫወት ወዘተ…
የሰላም ስጦታ
ሰዎች ብቻቸውን መሆን በሚፈልጉበት ሰዓት ብቻቸውን እንዲሆኑ በመፍቀድ (በመተው) ሰላማቸውን እንደስጦታ ይስጧቸው::
የበጎ ቃላት ስጦታ
መልካም ሰላምታ በመስጠት፤ ለተደረገልዎ ነገር ሁሉ ምስጋና በማቅረብ በመልካም ቃላትዎ የሰዎችንመልካም ስሜት ይጠብቁላቸው::
የሺፒንግና ሎጀስቲክስ ጆርናል (2004)