• የመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

የፀጉር መበጣጠስን ለማስቀረት


የፀጉር መበጣጠስን ለማስቀረት በሚል ውድ የውበት መጠበቂያና የፀጉር መንከባከቢያ ውጤቶችን ከመሸመት ይልቅ በቀላሉ የምናገኛቸውን ነገሮች እና


ተፈጥሯዊ ዘዴዎችን በመጠቀም ለፀጉራችን እንክብካቤ ማድረጉ የሚመረጥ ሲሆን፥ የውበት ባለሙያዎችም ይህንኑ እንድናደርግ ነው የሚመክሩን።

በመሆኑም እነዚህን አምስት አማራጮች እንድንተገብራቸው ታይምስ ኦፍ ኢንዲያ ያወጣው መረጃ ይመክራል።

1.ዘይት መጠቀም፣

የወይራ ዘይት፣ የኮኮናት ዘይት አልያም ሌላ ማንኛውንም አይነት ዘይት ወስደን እናፈላዋለን፤ ከዚያም ለብ ሲል በጥንቃቄ የፀጉራችንን ስር በደንብ እያዳረስን እንቀባዋለን፤ ለአንድ ሰዓት ያህልም በሻሽ ወይም ፎጣ ጠቅልለን ካቆየን በኋላ በሻምፖ እንለቃለቀዋለን።

2. ተፈጥሯዊ ጭማቂዎች (ጂውሶችን) መጠቀም፣

አመሻሽ ላይ የነጭ፣ ቀይ ሽንኩርት አልያም የዝንጅብል ጭማቂን ወስደን በተመሳሳይ የፀጉራችን ስሩን በደንብ መቀባት፤ ከዚያም በማግስቱ ልንለቃለቀው እንችላለን።

3. የጭንቅላት ማሳጅ (መታሸት)

የፀጉራችን ስር አካባቢ ለተወሰኑ ደቂቃዎች በየቀኑ የምናደርገው የማሸት (ማሳጅ) የማድረግ ተግባር የደም ዝውውርን የሚያቀላጥፍ ሲሆን፥ የደም ዝውውር መቀላጠፍም በአንፃሩ የፀጉር ሴሎችን እድገት ያነቃቃል።

4.አረንጓዴ ሻይ መጠቀም፣

ሁለት የአረንጓዴ ሻይ ከረጢት በአንድ ኩባያ የፈላ ውሃ ላይ በመጠቀም የፀጉራችንን የስረኛው ክፍል መቀባት፣ ለአንድ ሰዓት ያህል ካቆየነው በኋላም እንደምንፈልገው ልንለቃለቀው እንችላለን።

በአረንጓዴ ሻይ ውስጥ የምናገኘው አንቲኦክሲዳንትስ የፀጉር መነቃቀልን ይከላከላል።

በተጨማሪም የፀጉር ዕድገትን ያፋጥናል።

5. ጭንቀትን ማስወገድ፣

ለፀጉር መሳሳት እና መነቃቀል አብይ ምክንያት ተደርጎ የሚወሰደው ጭንቀት ነው።

በመሆኑም ከአላስፈላጊ ጭንቀት ራስን መከላከል እና የተመስጦ (ሜዲቴሽን) ተግባርን በማከናወን የፀጉር መነቃቀልንም ሆነ መሳሳትን መከላከል ይቻላል።

ተመስጦ በተጨማሪም የሆርሞን መመጣጠን እንዲኖር በማገዝ የፀጉር እድገት ፍጥነትን እንደሚጨምርም ነው የሚነገረው።

ምንጭ፦ zehabesha

#የፀጉርመበጣጠስንለማስቀረት

111 views0 comments

Copyright © 2018 Meskan Media Network - All Rights Reserved. E-mail : meskanmedia@gmail.com

  • YouTube - White Circle
  • White Spotify Icon
  • White Apple Music Icon
  • White Amazon Icon
  • White Facebook Icon
  • Twitter Clean