• የመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

ያልተማረ ይግደልህ


ያልተማረ ይግደልህ

ትናንትን አፈቀርኩት" ዛሬን ግን ጠላሁት

አፌን ለሆድ ብቻ ሲጮህ አገኘሁት፡፡

ትንሽ መግፋት ቢቻል ጊዜን ወደኋላ

እኔስ በተሰየምኩ ካባቴ ፊትለፊት ከአያቴ በኋላ

ወይ ታሪኬ ሊፃፍ ወይ ግፌ ሊሰላ፡፡

አባባ ገድልህን ለምን ነው የነገርከኝ?

ለትናንት አሻቅለህ ዛሬ አስጠላኸኝ

ብትከፍተው ገለባ

ሕይወት ትግል አልባ፣ትግሉም ሕይወት አልባ

የተማረ ይግደለኝ ብለህ አጓግተኸኝ

ፊደል ከቆጠረ ቁጥርን ከደመረ ለሆዱ ካደረ

መንጋ መሀል ጣልከኝ

እኔም ተማከርኩልህ" ተመራመርኩልህ

የመብት አቡጊዳ ትግሌን ጀመርኩልህ

መቀብሌን አትንኳት ብዬ ፎከርኩልህ

ኧረ በሞትኩልህ

ይልቅስ ልንገርህ" ሞትክን በተማረ መመኘትክን እርሳው

ጽድቁን ከፈለግከው

ፊደል ያልቆጠረው ያገሬ ገበሬ ተኩሶ ይጣልህ፣ይግደልህ ከማሳው፡፡


(ቼበለው መኩሪያ፣ ማለዳ፣ 1993)

38 views0 comments

Copyright © 2018 Meskan Media Network - All Rights Reserved. E-mail : meskanmedia@gmail.com

  • YouTube - White Circle
  • White Spotify Icon
  • White Apple Music Icon
  • White Amazon Icon
  • White Facebook Icon
  • Twitter Clean