- የመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ
ሐሳብ - ክፍል 5 (ኢዱና አህመድ)

ሃሳብን... በሃሳብ!
ሳስብ ስብሰለሰል በሃሳብ
ያ… ሃሳብ መጣና “የአህያ ባል” አለኝ በሃሳብ
እኔም በሃሳቤ ብዬ አልኩት
አወይ… አቅል ማጣት
አወይ… መንከራተት
ውል በጠፋው ውጥንሽ
በድረሱልኝ ብቻ ጽናትሽ
ፍሬ ሳያፈራ አፈርሳታሽ
መና አጣና በሬ ወለደሽ
በሰበቅ - ሰበቃው ጤዛው… ተነነ
ተረቱም… እውን ሆነ
የፈሩት ደረሰ!
የጠሉትም… ወረሰ!
ያ… አህያው ባልሽ
ከጅብ አላስጣለሽ!
አየሽ… አለማስተዋልሽ
ባንጠለጠለ ብቻ መለካትሽ
ስላንጠለጠለ… መኩራራትሽ
ቅንነት ባህላችን ነውና ምክርን ውሰጂ
አህያ መላ አያውቅም ልፋት ብቻ ቢሆን እንጂ!
ብሎ አለኝ ያ… ሃሳብ
…በሃሳብ….
ኢዱና አህመድ ኡስማን
ሪያድ ሳዑዲ አረቢያ
54 views0 comments